የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ቆሮንቶስ 7:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ መቄ​ዶ​ን​ያም በደ​ረ​ስን ጊዜ ለሰ​ው​ነ​ታ​ችን ጥቂት ስን​ኳን ዕረ​ፍት አላ​ገ​ኘ​ንም፤ በሁ​ሉም መከራ አጸ​ኑ​ብን እንጂ፤ በው​ጭም መጋ​ደል ነበር፤ በው​ስ​ጥም ፍር​ሀት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ መቄዶንያ በመጣን ጊዜ፣ ከየአቅጣጫው መከራ ደረሰብን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አላገኘም፤ ከውጭ ጠብ፣ ከውስጥ ደግሞ ፍርሀት ነበረብን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አልነበረውም፤ ከውጭ ጠብ ነበረ፤ ከውስጥ ደግሞ ፍርሃት ነበረብን።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መቄዶንያ በደረስን ጊዜ እንኳ ከብዙ አቅጣጫ ችግር ደረሰብን እንጂ ምንም ዕረፍት አላገኘንም፤ በውጭ ጠብ በውስጥም ፍርሀት ነበረብን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሥጋችን ዕረፍት አልነበረውም፤ በውጭ ጠብ ነበረ፥ በውስጥ ፍርሃት ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ቆሮንቶስ 7:5
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ርግብ እግ​ር​ዋን የም​ታ​ሳ​ር​ፍ​በት ስፍራ አላ​ገ​ኘ​ችም፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ተመ​ለ​ሰች፤ ውኃው በም​ድር ላይ ሁሉ ነበ​ረና፤ እጁን ዘረ​ጋና ተቀ​በ​ላት፤ ወደ እር​ሱም ወደ መር​ከብ ውስጥ አገ​ባት።


መከራ በዙ​ሪ​ያው ታጠ​ፋ​ዋ​ለች፤ ብዙ ጠላ​ቶ​ችም ከእ​ግሩ በታች ይመ​ጣሉ።


አሕ​ዛ​ብም በእ​ርሻ ውስጥ ተቈ​ርጦ እንደ ተጣ​ለና በእ​ሳት እንደ ተቃ​ጠለ እሾህ የተ​ቃ​ጠሉ ይሆ​ናሉ።”


በእኔ ላይ የተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና የከ​በ​ቡ​ኝን የብዙ ሰዎ​ችን ስድብ ሰም​ቻ​ለሁ፤ መው​ደ​ቄን የሚ​ጠ​ብቁ የሰ​ላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምና​ል​ባት ይታ​ለል እንደ ሆነ፥ እና​ሸ​ን​ፈ​ውም እንደ ሆነ፥ እር​ሱ​ንም እን​በ​ቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እን​ነ​ሣ​ለን” ይላሉ።


አንተ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ማሜ ላይ ኀዘ​ንን ጨም​ሮ​ብ​ኛ​ልና ወዮ​ልኝ! በል​ቅ​ሶዬ ጩኸት ደክ​ሜ​አ​ለሁ፤ ዕረ​ፍ​ት​ንም አላ​ገ​ኘ​ሁም ብለ​ሃል።


የጠ​ላት ሰይፍ ከብ​በ​ዋ​ች​ኋ​ልና ወደ ሜዳ አት​ውጡ፤ በመ​ን​ገ​ድም ላይ አት​ሂዱ።


ልባ​ች​ሁን ታም​ማ​ችሁ ትቅ​በ​ዘ​በ​ዛ​ላ​ችሁ። ከሚ​ያ​ቅ​በ​ዘ​ብዝ የልብ ሕመ​ማ​ችሁ የሚ​ያ​ድ​ና​ችሁ የለም።


ክር​ክ​ሩም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ጳው​ሎስ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን ጠራና አጽ​ና​ና​ቸው፤ ተሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወጥ​ቶም ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄደ።


መቄ​ዶ​ን​ያና አካ​ይያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅዱ​ሳን መካ​ከል ላሉ ድሆች አስ​ተ​ዋ​ጽ​ፅኦ ለማ​ድ​ረግ ተባ​ብ​ረ​ዋ​ልና።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሆ​ነ​ውና በእ​ና​ንተ ላይ ባለኝ ትም​ክ​ህት ሁል​ጊዜ እገ​ደ​ላ​ለሁ።


መቄ​ዶ​ን​ያም ደርሼ ወደ እና​ንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ በመ​ቄ​ዶ​ንያ በኩል አል​ፋ​ለ​ሁና።


ወን​ድ​ሜን ቲቶን ስላ​ላ​ገ​ኘ​ሁት ለሰ​ው​ነቴ ዕረ​ፍት አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ተለ​ይች ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄድሁ።


የእኔ ደስታ የሁ​ላ​ችሁ እንደ ሆነ በሁ​ላ​ችሁ አም​ኛ​ለ​ሁና በመ​ጣሁ ጊዜ ደስ ሊያ​ሰ​ኙኝ ከሚ​ገ​ባ​ቸው ኀዘን እን​ዳ​ያ​ገ​ኘኝ ይህን ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።


ስለ​ዚ​ህም በሁሉ ትታ​ዘ​ዙኝ እንደ ሆነ፥ ፈቃ​ዳ​ች​ሁን ዐውቅ ዘንድ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ።


ስለ እና​ንተ በከ​ንቱ ደክሜ እንደ ሆነ ብዬ እፈ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


ጐል​ማ​ሳ​ውን ከድ​ን​ግል፥ ሕፃ​ኑ​ንም ከሽ​ማ​ግሌ ጋር፥ በሜዳ ሰይፍ፥ በቤ​ትም ውስጥ ድን​ጋጤ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።


ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ “ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል፤ ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል፤” ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ።