የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ቆሮንቶስ 5:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለዚ​ህም ያዘ​ጋ​ጀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ እር​ሱም የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ ሰጠን።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለዚህ ዐላማ ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው፤ ሊመጣ ላለው ዋስትና እንዲሆነን መንፈሱን መያዣ አድርጎ የሰጠንም እርሱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለዚህም ነገር ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው፤ ከዚያም በላይ ለሚሰጠን ነገር ሁሉ ዋስትና እንዲሆን መንፈሱን የሰጠንም እርሱ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ቆሮንቶስ 5:5
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ልጆ​ቻ​ቸው የእ​ጄን ሥራ ባዩ ጊዜ ስለ እኔ ስሜን ይቀ​ድ​ሳሉ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ቅዱስ ይቀ​ድ​ሳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ ይፈ​ራሉ።


ሕዝ​ብሽ ሁሉ ጻድ​ቃን ይሆ​ናሉ፤ ምድ​ር​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይወ​ር​ሳሉ፤ እር​ሱ​ንም ለማ​መ​ስ​ገን የእ​ጆ​ቹን ሥራ ይጠ​ብ​ቃሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለክ​ብሩ የተ​ከ​ላ​ቸው የጽ​ድቅ ዛፎች እን​ዲ​ባሉ ለጽ​ዮን አል​ቃ​ሾች አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በአ​መ​ድም ፋንታ አክ​ሊ​ልን፥ በል​ቅ​ሶም ፋንታ የደ​ስ​ታን ዘይት፥ በኀ​ዘ​ንም መን​ፈስ ፋንታ የም​ስ​ጋ​ናን መጐ​ና​ጸ​ፊያ እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ልኮ​ኛል።


ነገር ግን የሚ​ተ​ክዝ ዓለም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ የተ​ቀ​በ​ል​ነው እናም ደግሞ እና​ዝ​ና​ለን እንጂ፤ የነ​ፍ​ሳ​ች​ንን ድኅ​ነት እና​ገኝ ዘንድ የል​ጅ​ነ​ትን ክብር ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንና፤ በእ​ም​ነ​ትም ድነ​ና​ልና።


ደግ​ሞም ያተ​መ​ንና የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ በል​ቡ​ና​ችን የሰ​ጠን እርሱ ነው።


ቀላል የሆ​ነው የጊ​ዜው መከ​ራ​ችን ክብ​ር​ንና ጌት​ነ​ትን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አብ​ዝቶ ያደ​ር​ግ​ል​ና​ልና።


እን​መ​ላ​ለ​ስ​በት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ላዘ​ጋ​ጀው በጎ ሥራ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የፈ​ጠ​ረን ፍጥ​ረቱ ነንና።


በዳ​ና​ችሁ ጊዜ የታ​ተ​ማ​ች​ሁ​በ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቅዱስ መን​ፈስ አታ​ሳ​ዝ​ኑት።


ትእዛዙንም የሚጠብቅ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በዚህም በእኛ እንዲኖር ከሰጠን ከመንፈሱ እናውቃለን።