የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ቆሮንቶስ 13:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ እና​ንተ ስመጣ እነሆ ይህ ሦስ​ተ​ኛዬ ነው፤ ነገር ሁሉ፥ በሁ​ለት ወይም በሦ​ስት ምስ​ክር አፍ የሚ​ጸና አይ​ደ​ለ​ምን?

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ መሆኑ ነው፤ “ነገር ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ስለሚጸና።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው። “ማንኛውም ነገር በሁለትና በሦስት ምስክር አፍ ይጸናል።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንግዲህ ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ መቼም ሁሉ ነገር የሚረጋገጠው በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ሁሉ ነገር በሁለትና በሦስት ምስክር አፍ ይጸናል።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ቆሮንቶስ 13:1
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ አንቺ በዚያ ለን​ጉሥ ስት​ነ​ግሪ እኔ ከአ​ንቺ በኋላ እገ​ባ​ለሁ፤ ቃል​ሽ​ንም አጸ​ና​ለሁ።”


ዳግ​መ​ኛም ወልደ አዴር እን​ዲህ ብሎ ወደ እርሱ ላከ፥ “ሕዝ​ቤና ሠራ​ዊቴ ሁሉ ሀገ​ር​ህን ሰማ​ር​ያን ባያ​ጠ​ፉት፥ የቀ​በ​ሮም ማደ​ሪያ ባያ​ደ​ር​ጉት አማ​ል​ክት እን​ዲህ ያድ​ር​ጉ​ብኝ፤ እን​ዲ​ህም ይግ​ደ​ሉኝ።”


እነ​ሆም፥ አንድ ነቢይ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ አክ​ዓብ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ሕዝብ ሁሉ ታያ​ለ​ህን? እነሆ፥ ዛሬ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ” አለው።


ነፍሰ ገዳይ ሁሉ በም​ስ​ክ​ሮች ቃል ይገ​ደ​ላል፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን ማና​ቸ​ው​ንም ሰው መግ​ደል አይ​ገ​ባም።


ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤


እነሆ ወደ እና​ንተ ልመጣ ስዘ​ጋጅ ይህ ሦስ​ተ​ኛዬ ነው፤ ነገር ግን አል​ተ​ፋ​ጠ​ን​ሁም ገን​ዘ​ባ​ች​ሁን ያይ​ደለ፥ እና​ን​ተን እሻ​ለ​ሁና፤ ልጆች ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ቸው ያይ​ደለ ወላ​ጆች ለል​ጆ​ቻ​ቸው ሊያ​ከ​ማቹ ይገ​ባ​ልና፤


በሁ​ለት ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ሞት የሚ​ገ​ባ​ቸው ይገ​ደሉ፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን አይ​ገ​ደሉ።


“ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማ​ድ​ረ​ግም ስለ​ሚ​ሠ​ራት ኀጢ​አት ሁሉ በማ​ንም ላይ አንድ ምስ​ክር አይ​ሁን፤ በሁ​ለት ምስ​ክ​ሮች ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ቃል ነገር ሁሉ ይጸ​ናል።