በሠላሳ ሁለት የአህያ ግልገሎች ይቀመጡ የነበሩ ሠላሳ ሁለት ልጆችም ነበሩት፤ ለእነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች የተባሉ በገለዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተሞች ነበሩአቸው።
1 ሳሙኤል 9:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦልም አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፥ “ከብላቴኖቹ አንዱን ወስደህ ተነሡና ሄዳችሁ አህዮችን ፈልጉ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ጊዜ የሳኦል አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፣ “ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልግ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ጊዜ የሳኦል አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፤ ቂስም ልጁን ሳኦልን፥ “ከአገልጋዮቹ መካከል አንዱን ይዘህ ሂድና አህዮቹን ፈልግ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳኦል አባት ቂስ፥ አህዮቹ ጠፍተውበት ነበር፤ ስለዚህም ልጁን ሳኦልን “ከአገልጋዮች አንዱን ይዘህ ሂድና የጠፉትን አህዮች ፈልግ” ብሎ አዘዘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም አባት የቂስ አህዮች ጠፍተው ነበር፥ ቂስም ልጁን ሳኦልን፦ ከብላቴኖቹ አንዱን ወስደህ ተነሣ፥ አህዮችንም ለመሻት ሂድ አለው። |
በሠላሳ ሁለት የአህያ ግልገሎች ይቀመጡ የነበሩ ሠላሳ ሁለት ልጆችም ነበሩት፤ ለእነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች የተባሉ በገለዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ሁለት ከተሞች ነበሩአቸው።
ከቤተ ሰቡም አንዱ እርሱንና ብላቴናውን፥ “ወዴት ሄዳችሁ ኖሮአል?” አላቸው። እነርሱም፥ “አህዮችን ልንፈልግ ሄደን ነበር፤ ባጣናቸውም ጊዜ ወደ ሳሙኤል መጣን” አሉት።
ዛሬ ከእኔ በተለየህ ጊዜ በብንያም ግዛት በቤቴል አውራጃ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች እየቸኰሉ ሲሄዱ ታገኛለህ፤ እነርሱም፦ ልትፈልጉአቸው ሂዳችሁ የነበራችሁላቸው አህዮች ተገኝተዋል፤ እነሆም፥ አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰብ ትቶ፦ የልጄን ነገር እንዴት አደርጋለሁ? እያለ ስለ እናንተ ይጨነቃል ይሉሃል።
ለእርሱም ሳኦል የሚባል የተመረጠ መልካም ልጅ ነበረው፤ በምድር ሁሉ ላይ ከእስራኤል ልጆች ከእርሱ ይልቅ መልካም የሆነ ሰው አልነበረም፤ ከሕዝቡም ሁሉ ይልቅ ከትከሻውና ከዚያም በላይ ቁመቱ ዘለግ ያለ ነበረ።
ከሦስት ቀንም በፊት የጠፉ አህዮችህ ተገኝተዋልና ልብህን አታስጨንቀው። የእስራኤል መልካም ምኞት ለማን ነው? ለአንተና ለአባትህ ቤት አይደለምን?” አለው።
ወደ ተራራማውም ወደ ኤፍሬም ሀገር ሄዱ፤ በሲልካ ምድርም አለፉ፤ አላገኙአቸውምም፤ በፋስቂም ምድር አለፉ፤ በዚያም አልነበሩም፤ በኢያሚንም ምድር አለፉ፤ አላገኙአቸውምም።