የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 31:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ወጉ፤ እስራኤላውያንም ከፊታቸው ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ተወግተው ወደቁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ወጉ፤ እስራኤላውያንም ከፍልስጥኤማውያን ፊት፥ በጊልቦዓ ተራራ ላይ የወደቁትን ጥለው ሸሹ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፍልስጥኤማውያን በጊልቦዓ ተራራ ከእስራኤላውያን ጋር ጦርነት ገጠሙ፤ ብዙ እስራኤላውያንም ሸሹ፤ ብዙዎችም ተገደሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፥ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ ተወግተውም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወደቁ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 31:1
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ንተ የጌ​ላ​ቡሄ ተራ​ሮች ሆይ፥ ዝና​ብና ጠል አይ​ው​ረ​ድ​ባ​ችሁ፤ ቍር​ባ​ን​ንም የሚ​ያ​በ​ቅል እርሻ አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ። የኀ​ያ​ላን ጋሻ በዚያ ወድ​ቆ​አ​ልና፤ የሳ​ኦ​ልም ጋሻ ዘይት አል​ተ​ቀ​ባ​ምና።


ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለት ጎል​ማ​ሳም አለ፥ “በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ተዋ​ግ​ተው ወደቁ፤ እነ​ሆም፥ ሳኦል በጦሩ ላይ ተኝቶ ነበር፤ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ተከ​ት​ለው ደረ​ሱ​በት።


ለሳ​ኦ​ልም ልጅ ለዮ​ና​ታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበ​ረው። የሳ​ኦ​ልና የዮ​ና​ታን ወሬ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል በመጣ ጊዜ የአ​ም​ስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግ​ዚ​ቱም አዝ​ላው ሸሸች፤ ልት​ሸ​ሽም ስት​ሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ነበረ።


ነገር ግን ክፉ ብት​ሠሩ እና​ን​ተም፥ ንጉ​ሣ​ች​ሁም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ።”


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዚያ ወራት ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይዋጉ ዘንድ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ለሰ​ልፍ ሰበ​ሰቡ፤ አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “አን​ተና ሰዎ​ችህ ከእኔ ጋር ወደ ሰልፍ እን​ድ​ት​ወጡ በር​ግጥ ዕወቅ” አለው።


ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “ለምን አወ​ክ​ኸኝ? ለም​ንስ አስ​ነ​ሣ​ኸኝ?” አለው። ሳኦ​ልም መልሶ፥ “ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ይወ​ጉ​ኛ​ልና እጅግ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእኔ ርቆ​አል፤ በነ​ቢ​ያት ወይም በሕ​ልም አላ​ሚ​ዎች አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም፤ ስለ​ዚ​ህም የማ​ደ​ር​ገ​ውን ታስ​ታ​ው​ቀኝ ዘንድ ጠራ​ሁህ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን ከአ​ንተ ጋር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፤ ነገም አን​ተና ከአ​ንተ ጋር ያሉ ልጆ​ችህ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጭፍራ ደግሞ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ፤ በሱ​ነ​ምም ሰፈሩ፤ ሳኦ​ልም እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ በጌ​ላ​ቡ​ሄም ሰፈሩ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበ​ሰቡ፤ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ።