የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 20:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮና​ታ​ንም፥ “ይህ ከአ​ንተ ይራቅ፤ ከአ​ባቴ ዘንድ ክፋት በላ​ይህ እንደ ተቈ​ረ​ጠች ያወ​ቅሁ እንደ ሆነ በከ​ተማ ባት​ኖ​ርም እን​ኳን ወደ አንተ መጥቼ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዮናታንም፣ “ይህ ከአንተ ይራቅ! አባቴ ክፉ ነገር እንዳሰበብህ ባውቅ ኖሮ እንዴት ሳልነግርህ እቀራለሁ?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮናታንም፥ “ይህ ከአንተ ይራቅ! አባቴ ክፉ ነገር እንዳሰበብህ ባውቅ ኖሮ እንዴት ሳልነግርህ እቀራለሁ?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮናታን ግን “እንዲህ ያለውን ነገር ፈጽሞ አታስብ! በአንተ ክፉ ነገር አስቦ ቢሆን ኖሮ፥ እነግርህ አልነበረም?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮናታንም፦ ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ከአባቴ ዘንድ ክፋት በላይህ እንደ ተቆረጠች ያወቅሁ እንደ ሆነ አልነግርህምን? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 20:9
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮና​ታ​ንም፥ “አባቴ ሳኦል ሊገ​ድ​ልህ ፈል​ጎ​አል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ለነ​ገው ተጠ​ን​ቅ​ቀህ ተሸ​ሸግ፤ በስ​ው​ርም ተቀ​መጥ።


እኔም እወ​ጣ​ለሁ፤ አን​ተም ባለ​ህ​በት እርሻ በአ​ባቴ አጠ​ገብ እቆ​ማ​ለሁ፤ ስለ አን​ተም ለአ​ባቴ እነ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ፤ የሆ​ነ​ው​ንም አይቼ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” ብሎ ለዳ​ዊት ነገ​ረው።


ዳዊ​ትም ዮና​ታ​ንን፥ “አባ​ትህ ስለ እኔ ክፉ ነገር የነ​ገ​ረህ እንደ ሆነ ማን ይነ​ግ​ረ​ኛል?” አለው።


ዮና​ታ​ንም ደግሞ፥ “ቶሎ ፍጠን፤ አት​ቈይ” ብሎ ወደ ብላ​ቴ​ናው ጮኸ፤ የዮ​ና​ታ​ንም ብላ​ቴና ፍላ​ጻ​ዎ​ቹን ሰብ​ስቦ ወደ ጌታው መጣ።


ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “በሰ​ላም ሂድ፤ እነሆ፥ እኛ ሁለ​ታ​ችን በእ​ኔና በአ​ንተ፥ በዘ​ሬና በዘ​ርህ መካ​ከል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ምስ​ክር ይሁን ብለን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ተማ​ም​ለ​ናል” አለው። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ዮና​ታ​ንም ወደ ከተማ ገባ።


እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ከባ​ሪ​ያህ ጋር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ለባ​ሪ​ያህ ቸር​ነ​ትን አድ​ርግ፤ በደል ግን ቢገ​ኝ​ብኝ አንተ ግደ​ለኝ፤ ለምን ወደ አባ​ትህ ታደ​ር​ሰ​ኛ​ለህ?”