የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 17:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳኦ​ልና የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎ​ችም ተሰ​በ​ሰቡ፤ በኤላ ሸለ​ቆም ሰፈሩ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ሊዋጉ ተሰ​ለፉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳኦልና እስራኤላውያን ተሰብስበው፣ በኤላ ሸለቆ ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንንም ለመግጠም ቦታ ቦታቸውን ያዙ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦልና እስራኤላውያን ደግሞ ተሰብስበው በዔላ ሸለቆ ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንንም ለመግጠም ተሰለፉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳኦልና እስራኤላውያንም ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት በተዘጋጁበት በኤላ ሸለቆ ተሰብስበው መሸጉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ተከማቹ፥ በዔላ ሸለቆም ሰፈሩ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ሊዋጉ ተሰለፉ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 17:2
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሳኦ​ልና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር እየ​ተ​ዋጉ በኤላ ሸለቆ ነበሩ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በአ​ንድ ወገን በተ​ራራ ላይ ቆመው ነበር፥ እስ​ራ​ኤ​ልም በሌ​ላው ወገን በተ​ራራ ላይ ቆመው ነበር፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ሸለቆ ነበረ።


ዳዊ​ትም ተነሣ በዚ​ያም ቀን ከሳ​ኦል ፊት ሸሸ፤ ወደ ጌትም ንጉሥ ወደ አን​ኩስ መጣ።


ካህ​ኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገ​ደ​ል​ኸው የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው የጎ​ል​ያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጠ​ቅ​ልላ አለች፤ የም​ት​ወ​ስ​ዳት ከሆነ ውሰ​ዳት፤ ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለ​ምና” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው። እር​ሱም ሰጠው።