ዳዊትም ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ገዦች መልእክተኞችን ላከ፤ ዳዊትም እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ እግዚአብሔር ለቀባው ለጌታችሁ ለሳኦል ይህን ቸርነት አድርጋችኋልና፥ እርሱንና ልጁን ዮናታንንም ቀብራችኋቸዋልና በእግዚአብሔር የተባረካችሁ ሁኑ።
1 ሳሙኤል 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመጡትንም መልእክተኞች፥ “የኢያቢስ ገለዓድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተኰሰ ጊዜ ድኅነት ይሆንላችኋል በሉአቸው” አሉአቸው። መልእክተኞችም ወደ ከተማዪቱ መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሩ፤ ደስም አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፣ “ለኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች፣ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለኢያቢስ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ በደስታ ፈነደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ ለመጡትም መልእክተኞች፥ “ለያቢሽ ገለዓድ ሰዎች፥ ‘ነገ ፀሓይ ሞቅ በሚልበት ጊዜ ነጻ ትሆናላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው” አሏቸው። መልእክተኞቹም ሄደው ለያቢሽ ሰዎች ይህንኑ በነገሯቸው ጊዜ እጅግ ተደሰቱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከያቤሽ የመጡትንም መልእክተኞች “ነገ ከቀትር በፊት የምናድናቸው መሆኑን ለሕዝባችሁ ንገሩ” አሉአቸው። መልእክቱንም ለያቤሽ ሰዎች በነገሩ ጊዜ የያቤሽ ሰዎች እጅግ ተደሰቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመጡትንም መልክተኞች፦ የኢያቢስ ገለዓድን ሰዎች፦ ነገ ፀሐይ በተኮሰ ጊዜ ማዳን ይሆንላችኋል በሉአቸው አሉአቸው። መልክተኞችም መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሩ፥ ደስም አላቸው። |
ዳዊትም ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ገዦች መልእክተኞችን ላከ፤ ዳዊትም እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ እግዚአብሔር ለቀባው ለጌታችሁ ለሳኦል ይህን ቸርነት አድርጋችኋልና፥ እርሱንና ልጁን ዮናታንንም ቀብራችኋቸዋልና በእግዚአብሔር የተባረካችሁ ሁኑ።
ጽኑዓን ሰዎች ሁሉ ከገለዐድ ተነሥተው የሳኦልን ሬሳ የልጆቹንም ሬሳዎች ወሰዱ፥ ወደ ኢያቢስም አመጡአቸው፤ በኢያቢስም ካለው ከትልቁ ዛፍ በታች አጥንቶቻቸውን ቀበሩ፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።
እነርሱም፥ “ከእስራኤል ነገድ ወደ እግዚአብሔር ወደ መሴፋ ያልወጣ ማን ነው?” አሉ። እነሆም፥ ከኢያቢስ ገለዓድ ወደ ሰፈሩ ወደ ጉባኤው ማንም አልወጣም ነበር።
ፍልስጥኤማውያንም በሳኦል ላይ ያደረጉትን የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች በሰሙ ጊዜ፥ ጀግኖች ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ሄዱ፥