ሕዝቅያስንም አትስሙ፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ በሕይወት ልትኖሩ ብትወድዱ ሁላችሁ ወደ እኔ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ትጠጣላችሁ፤
1 ሳሙኤል 11:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢያቢስም ሰዎች፥ “ወደ እስራኤል ሀገር ሁሉ መልእክተኞችን እንድንልክ ሰባት ቀን ቈይልን፤ ከዚያም በኋላ የሚያድነን ባይኖር ወደ አንተ እንመጣለን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢያቢስም ሽማግሌዎች፣ “ወደ መላው እስራኤል መልእክተኞችን እንድንልክ የሰባት ቀን ጊዜ ስጠን፤ ሊታደገን የሚመጣ ሰው ከሌለ፣ ለአንተ እንገዛለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያቢሽም ሽማግሌዎች፥ “ወደ መላው እስራኤል መልእክተኞችን እንድንልክ የሰባት ቀን ጊዜ ስጠን፤ ሊታደገን የሚመጣ ሰው ከሌለ ለአንተ እንገዛለን” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያቤሽ መሪዎችም “ወደ መላው የእስራኤል ምድር መልእክተኞች እስክንልክ ድረስ የሰባት ቀን ጊዜ ስጠን፤ እኛን የሚታደገን ካጣን ለአንተ እጃችንን እንሰጣለን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢያቢስም ሽማግሌዎች፦ ወደ እስራኤል አገር ሁሉ መልክተኞችን እንድንልክ ሰባት ቀን ቆይልን፥ ከዚያም በኋላ የሚያድነን ባይኖር ወደ አንተ እንመጣለን አሉት። |
ሕዝቅያስንም አትስሙ፤ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ በሕይወት ልትኖሩ ብትወድዱ ሁላችሁ ወደ እኔ ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ትበላላችሁ፤ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ትጠጣላችሁ፤