የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰላ​ም​ታም ይሰ​ጡ​ሃል፤ የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን ሁለት ዳቦ​ዎ​ችም ይሰ​ጡ​ሃል፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም ትቀ​በ​ላ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም ሰላም ይሉሃል፤ ሁለት ዳቦ ይሰጡሃል፤ አንተም ትቀበላቸዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም ሰላም ይሉሃል፤ ሁለት ዳቦ ይሰጡሃል፤ አንተም ከእጃቸው ትቀበላለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ሰላምታ ከሰጡህ በኋላ ከኅብስቶቹ ሁለቱን ይሰጡሃል፤ አንተም መቀበል ይገባሃል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰላምታም ይሰጡሃል፥ ሁለትም ዳቦ ይሰጡሃል፥ ከእጃቸውም ትቀበላለህ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 10:4
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከመ​ን​ገ​ዱም ፈቀቅ ብለው ወደ ጐል​ማ​ሳው ሌዋዊ ቤት ወደ ሚካ ቤት መጡ፤ ሰላ​ም​ታም ሰጡት።


ከዚ​ያም ደግሞ አል​ፈህ፥ ወደ ትልቁ የታ​ቦር ዛፍ ትደ​ር​ሳ​ለህ፤ በዚ​ያም ሦስት ሰዎች፥ አንዱ ሦስት የፍ​የል ጠቦ​ቶች ሲነዳ፥ ሁለ​ተ​ኛው ሦስት የዳቦ ስልቻ፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም የወ​ይን ጠጅ አቁ​ማዳ ይዘው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ቤቴል ሲወጡ ታገ​ኛ​ለህ፤


ከዚ​ያም በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ ወዳ​ለ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኮረ​ብታ ትመ​ጣ​ለህ፤ በዚ​ያም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ናሴብ አለ፤ ወደ​ዚ​ያም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በደ​ረ​ስህ ጊዜ በገ​ናና ከበሮ፥ እም​ቢ​ል​ታና መሰ​ንቆ ይዘው ትን​ቢት እየ​ተ​ና​ገሩ ከኰ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ የሚ​ወ​ርዱ የነ​ቢ​ያ​ትን ጉባኤ ታገ​ኛ​ለህ።


እሴ​ይም እን​ጀ​ራና የወ​ይን ጠጅ አቁ​ማዳ የተ​ጫነ አህያ፥ አን​ድም የፍ​የል ጠቦት ወስዶ በልጁ በዳ​ዊት እጅ ወደ ሳኦል ላከ።