የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ነገሥት 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ካህ​ና​ቱም ታቦ​ቷን አነሡ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በመጡ ጊዜ፣ ካህናቱ ታቦቱን አነሡ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

መሪዎቹ ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜም ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አንሥተው ተሸክሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መሪዎቹ ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜም ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት አንሥተው ተሸክሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ፤ ካህናቱም ታቦቱን አነሡ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ነገሥት 8:3
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለን​ጉሡ ዳዊ​ትም “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ቢ​ዳ​ራን ቤትና የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገ​ሩት። ዳዊ​ትም ሄዶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከአ​ቢ​ዳራ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደ​ስታ አመ​ጣት።


ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት በቤቱ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ውስጥ ከኪ​ሩ​ቤል ክንፍ በታች ወደ ነበ​ረው ወደ ስፍ​ራዋ አገቧት።


በዚ​ያን ጊዜም ዳዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይሸ​ከሙ ዘንድ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ረ​ጣ​ቸው ከሌ​ዋ​ው​ያን በቀር ማንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ይሸ​ከም ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም” አለ።


አሮ​ንና ልጆቹ መቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍ​ነው ከጨ​ረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀ​ዓት ልጆች ሊሸ​ከ​ሙት ይገ​ባሉ። እን​ዳ​ይ​ሞቱ ግን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን አይ​ንኩ። በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።


ለቀ​ዓት ልጆች ግን መቅ​ደ​ሱን ማገ​ል​ገል የእ​ነ​ርሱ ነውና፥ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ይሸ​ከ​ሙት ነበ​ርና ምንም አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።


ሙሴም ይህ​ችን ሕግ ጻፈ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ይሸ​ከሙ ለነ​በ​ሩት ለሌዊ ልጆች ለካ​ህ​ናቱ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ሰጣት።


ለሕ​ዝ​ቡም እን​ዲህ ብለው ዐወጁ፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ሌዋ​ው​ያ​ንና ካህ​ናት ተሸ​ክ​መ​ውት ባያ​ችሁ ጊዜ፥ ከሰ​ፈ​ራ​ችሁ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ተከ​ተ​ሉት።


ኢያ​ሱም ካህ​ና​ቱን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​ማ​ችሁ በሕ​ዝቡ ፊት ሂዱ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​መው በሕ​ዝቡ ፊት ሄዱ።


ኢያ​ሱም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግ​ሮች በቆ​ሙ​በት ስፍራ በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ሌሎች ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን አቆመ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።


የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ከሙ፤ ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት ወስ​ደው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላ​ቸው።