የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ነገሥት 6:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ወለል ነበረ፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ መቅ​ደሱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ከቤቱ ወደ ፊት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ ቤቱ​ንም ሠርቶ ጨረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በቤተ መቅደሱ አዳራሽ ፊት ለፊት ያለው በረንዳ ወርዱ እንደ ቤተ መቅደሱ ወርድ ሁሉ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ርዝመቱ ዐሥር ክንድ ወደ ውጭ የወጣ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመግቢያው በር የሚገኘው በረንዳ ቁመቱ አራት ሜትር ተኩል፥ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ዘጠኝ ሜትር ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመግቢያው በር የሚገኘው በረንዳ ቁመቱ አራት ሜትር ተኩል፥ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ዘጠኝ ሜትር ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመቅደሱም ፊት ወለል ነበረ፤ ርዝመቱም እንደ መቅደሱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወርዱም ከቤቱ ወደፊት ዐሥር ክንድ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ነገሥት 6:3
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሠ​ራው ቤት ርዝ​መቱ ስድሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ።


ለቤ​ቱም በዐ​ይነ ርግብ የተ​ዘጉ መስ​ኮ​ቶ​ችን አደ​ረገ።


በታ​ላ​ቁም አደ​ባ​ባይ ዙሪያ የነ​በ​ረው ቅጥር እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ቅጥ​ርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ወገን በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ አን​ዱም ወገን በዝ​ግባ ሳንቃ ተሠ​ርቶ ነበር።


አዕ​ማ​ዱ​ንም በመ​ቅ​ደሱ ወለል አጠ​ገብ አቆ​ማ​ቸው፤ የቀ​ኙ​ንም ዓምድ አቁሞ ያቁም ብሎ ጠራው፤ የግ​ራ​ው​ንም ዓምድ አቁሞ በለዝ ብሎ ጠራው።


ዳዊ​ትም ለመ​ቅ​ደሱ ወለል፥ ለቤ​ቱም፥ ለቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም፥ ለደ​ር​ቡና ለው​ስ​ጡም ጓዳ​ዎች፥ ለስ​ር​የ​ቱም መክ​ደኛ መቀ​መጫ ምሳ​ሌ​ውን ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።


ወደ ቤቱም ደጀ ሰላም አመ​ጣኝ፤ የደጀ ሰላ​ሙ​ንም የግ​ንብ አዕ​ማድ ወርድ በዚህ ወገን አም​ስት ክንድ፤ በዚ​ያም ወገን አም​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የበ​ሩም ወርድ ዐሥራ አራት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም በዚህ ወገ​ንና በዚያ ወገን የነ​በ​ሩት ግን​ቦች ሦስት ሦስት ክንድ ነበሩ።


ወደ​ኋ​ላ​ውም በአ​ለው በልዩ ስፍራ አን​ጻር የነ​በ​ረ​ውን የግ​ቢ​ውን ርዝ​መት፥ በዚ​ህና በዚያ ከነ​በ​ሩት ከግ​ን​ቦቹ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የው​ስ​ጡ​ንም መቅ​ደስ፥ የአ​ዳ​ራ​ሹ​ንም መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎች ለካ።


ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ በሰ​ሎ​ሞን ደጅ መመ​ላ​ለሻ ይመ​ላ​ለስ ነበር።