የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ነገሥት 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዳ​ዊት አሽ​ከ​ሮ​ችም፥ “ለጌ​ታ​ችን ለን​ጉሡ ድን​ግል ልጅ ትፈ​ለ​ግ​ለት፤ በን​ጉ​ሡም ፊት ቆማ ታገ​ል​ግ​ለው፥ በጌ​ታ​ች​ንም በን​ጉሡ ብብት ተኝታ ትቀ​ፈው፤ ታሙ​ቀ​ውም” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ አገልጋዮቹ፣ “ንጉሡን የምትንከባከብና የምታገለግል ወጣት ድንግል እንፈልግ፤ እርሷም ጌታችን ንጉሡ እንዲሞቀው በጐኑ ትተኛለች” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ባርያዎቹም፦ “ንጉስ ሆይ! ከአንተ ጋር ሆና የምትንከባከብህ ወጣት ልጃገረድ ፈልገን እናምጣ፤ በጌታችንም በንጉሡ እቅፍ ተኝታ ታሞቅሃለች” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ባለሟሎቹ “ንጉሥ ሆይ! ከአንተ ጋር ሆና የምትንከባከብህ ወጣት ልጃገረድ ፈልገን እናምጣልህ፤ ከአንተ ጋር ዐቅፋህ በመተኛት ታሞቅሃለች” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ባሪያዎቹም “ለጌታችን ለንጉሡ ድንግል ትፈለግለት፤ በንጉሡም ፊት ቆማ ታገልግለው፤ በጌታችንም በንጉሡ ብብት ተኝታ ታሙቀው፤” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ነገሥት 1:2
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሦራም አብ​ራ​ምን፥ “ከአ​ንተ የተ​ነሣ እገ​ፋ​ለሁ፤ እኔ አገ​ል​ጋ​ዬን በብ​ብ​ትህ ሰጠ​ሁህ፤ እንደ ፀነ​ሰ​ችም ባየች ጊዜ እኔን ማክ​በ​ርን ተወች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ይፍ​ረድ” አለ​ችው።


ለድ​ሃው ግን ከገ​ዛት አን​ዲት ታናሽ በግ በቀር አን​ዳች አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ አሳ​ደ​ጋ​ትም፤ ተን​ከ​ባ​ከ​ባ​ትም፤ ከእ​ር​ሱና ከል​ጆቹ ጋር አደ​ገች፤ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ትበላ፥ ከዋ​ን​ጫ​ውም ትጠጣ፥ በብ​ብ​ቱም ትተኛ ነበረ፤ እንደ ልጁም ነበ​ረች።


ንጉሡ ዳዊ​ትም አረጀ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ ልብ​ስም ይደ​ር​ቡ​ለት ነበር፤ ነገር ግን አይ​ሞ​ቀ​ውም ነበር።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር ሁሉ የተ​ዋ​በች ቆንጆ ፈለጉ፤ ሱነ​ማ​ዪ​ቱን አቢ​ሳ​ንም አገኙ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወሰ​ዱ​አት።


አሁ​ንም በፊቱ ትቆ​ሙና ታገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥ​ኑ​ለ​ትም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​አ​ች​ኋ​ልና ቸል አት​በሉ።”


ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ቢተኙ ይሞ​ቃ​ቸ​ዋል፤ አንድ ብቻ​ውን ግን እን​ዴት ይሞ​ቀ​ዋል?


ባልንጀራን አትመኑ፥ በወዳጅም አትታመኑ፥ የአፍህን ደጅ በብብትህ ከምትተኛው ጠብቅ።


በዚ​ያን ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸ​ከም ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ለማ​ገ​ል​ገል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይቆም ዘንድ፥ በስ​ሙም ይባ​ርክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስከ ዛሬ ድረስ የሌ​ዊን ነገድ ለየ።


“የአ​ባ​ትህ ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ ወን​ድ​ምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብ​ራህ የም​ት​ተኛ ሚስ​ትህ ወይም እንደ ነፍ​ስህ ያለ ወዳ​ጅህ በስ​ውር፦ ና፥ ሄደን አን​ተም አባ​ቶ​ች​ህም የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብሎ ቢያ​ስ​ትህ፥