ከዚህም ከሠላሳ ዓመት በኋላ እግዚአብሔር የባሪያውን ልመና ሰማ፤ መከራዬንም አየ፤ ድካሜንና ሥቃዬን ተመልክቶ አንድ ልጅ ሰጠኝ፤ በእርሱም ፈጽሞ ደስ አለኝ፤ እኔም፥ ባሌም፥ ያገሬም ሰዎች ሁሉ ደስ አለን፤ እግዚአብሔርንም አመሰገንነው።