ያንጊዜ የዚያ የዘሩ፥ የዚያም የመርከቡ፥ የዚያም የመብሉና የመጠጡ ይጠፋ ዘንድ ጊዜው ቢሆን እንደዚሁ የሚጠፋ ይሆናል። ነገር ግን የያዙት ይቀራሉ። ለእኛስ እንደዚሁ አይደለም። ሕግን ተቀብለን የበደልን እኛ እንጠፋለንና፥ የተቀበለው ልባችንም እንዲሁ ነው፤ ሕጉ ግን በክብሩ ይኖራል እንጂ አይጠፋም።”