እኔም መለስሁለት እንዲህም አልሁት፥ “በፊትህ ባለሟልነትን ካገኘሁ ይህንም ለባሪያህ ንገረው፤ በሞትን ጊዜ፥ ከእኛ ከእያንዳንዳችንም ነፍሳችን በምትወጣበት ጊዜ ቍርጥ ፍርዱን የሚያደርግበት ጊዜው እስኪደርስ ድረስ ይጠብቁናል? ወይስ ከዛሬ ጀምሮ ይፈረድብናል?”