አምስተኛዪቱም ሥርዐት እንዲህ ናት፤ ዛሬ ያለውን ሞት እንዴት ድል እንደነሡትና ኋላ ያገኙት ዘንድ ያላቸውን እንደ ወረሱ አይተው ደስ ይላቸዋልና፤ ዳግመኛም ድካምን ከተመላ ከዚህ ከጠባቡ የተነሣ እንደታገሡ፥ ያን ሰፊውን ሕይወት እንደሚያገኙ ያያሉ። ሞት በሌለበትም ለዘለዓለም ደስ ይላቸዋል።