ከነገርሁህ ሥርዐታት ሁሉ የምትበልጥ ሰባተኛዪቱ ሥርዐት እንዲህ ናት፤ በፊቱ ይፈረድባቸው ዘንድ ያላቸው ዛሬ በሕይወታቸው ሳሉ እርሱን የበደሉ በፊታቸው የልዑልን ጌትነት ባዩ ጊዜ በኀሣር ይቀልጣሉና፥ በኀፍረትም ይጐሳቈላሉና፥ በፍርሀትም ይጠወልጋሉና።