የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ቆሮንቶስ 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ገን​ዘ​ቤን ሁሉ ለም​ጽ​ዋት ብሰጥ፥ ሥጋ​ዬ​ንም ለእ​ሳት መቃ​ጠል ብሰጥ፥ ነገር ግን ፍቅር ከሌ​ለኝ ምንም አይ​ጠ​ቅ​መ​ኝም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ያለኝን ሁሉ ለድኾች ብሰጥ፣ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ለእሳት ብዳርግ፣ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያለኝን ሁሉ ለድኾች ባካፍል፥ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ለእሳት አሳልፌ ብሰጥ፥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያለኝን ሁሉ ለድኾች ባካፍል፥ ሥጋዬም እንኳ ሳይቀር በእሳት እንዲቃጠል አሳልፌ ብሰጥ፥ ፍቅር ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ቆሮንቶስ 13:3
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ግ​ዲህ እኔ ጽድ​ቄ​ንና የማ​ይ​ረ​ባ​ሽን የአ​ን​ቺን በደል እና​ገ​ራ​ለሁ።


“እነሆ በማ​ት​ጠ​ቀ​ሙ​በት በሐ​ሰት ቃል ብት​ተ​ማ​መ​ኑም፤


ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ሰምቶ እን​ዲህ አለው፥ “አን​ዲት ቀር​ታ​ሃ​ለች፤ ሂድና ያለ​ህን ሁሉ ሸጠህ ለነ​ዳ​ያን ስጥ፤ በሰ​ማ​ይም መዝ​ገብ ታገ​ኛ​ለህ፤ መጥ​ተ​ህም ተከ​ተ​ለኝ።”


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከ​ት​ለ​ን​ሃል፤ እን​ግ​ዲህ ምን እና​ገ​ኛ​ለን?” አለው።


ዘኬ​ዎ​ስም ቆመና ጌታ​ች​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አሁን የገ​ን​ዘ​ቤን እኩ​ሌታ ለነ​ዳ​ያን እሰ​ጣ​ለሁ፤ የበ​ደ​ል​ሁ​ትም ቢኖር ስለ አንድ ፋንታ አራት እጥፍ እከ​ፍ​ለ​ዋ​ለሁ።”


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ይልቅ የሰ​ውን ክብር ወደ​ዋ​ልና።


ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ ምን አሁን ልከ​ተ​ልህ አል​ች​ልም? እኔ ነፍ​ሴ​ንም እንኳ ቢሆን ስለ አንተ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ” አለው።


ስለ ወዳ​ጆቹ ሕይ​ወ​ቱን አሳ​ልፎ የሚ​ሰጥ ሰው ያለ እንደ ሆነ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ፍቅር የለም።


ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ መን​ፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አን​ዳች አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ ይህም እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ቃል መን​ፈስ ነው፤ ሕይ​ወ​ትም ነው።


ጳው​ሎስ ግን መልሶ፥ “ለምን እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እያ​ለ​ቀ​ሳ​ችሁ ልቤን ትሰ​ብ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ፤ እኔ እኮ ተስፋ የማ​ደ​ር​ገው መከ​ራ​ንና እግር ብረ​ትን ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሞ​ትም ቢሆን የቈ​ረ​ጥሁ ነኝ” አለ።


ኩሩ​ዎች አን​ሁን፤ እርስ በር​ሳ​ችን አን​ተ​ማማ፤ እርስ በር​ሳ​ች​ንም አን​ቀ​ናና።


በክ​ር​ክ​ርና ከንቱ ውዳ​ሴን በመ​ው​ደድ አት​ሥሩ፤ ትሕ​ት​ናን በያዘ ልቡና ከራ​ሳ​ችሁ ይልቅ ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁን አክ​ብሩ እንጂ አት​ታ​በዩ።


ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።


ሌላ ልዩ ትም​ህ​ርት አታ​ምጡ፤ ልባ​ችሁ በመ​ብል ያይ​ደለ በጸጋ ቢጸና ይበ​ል​ጣ​ልና፤ በዚያ ይሄዱ የነ​በሩ እነ​ዚያ አል​ተ​ጠ​ቀ​ሙ​ምና።