“መቼም ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፣ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና የክንዱን አንባር ወስጄ እነሆ፤ ለጌታዬ አምጥቻለሁ።”
2 ሳሙኤል 1:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚያም፣ ‘እኔ በሞት ጣር ውስጥ እገኛለሁ፤ ነፍሴ ግን አልወጣችም፤ እባክህ በላዬ ቆመህ ግደለኝ’ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም፥ ‘እኔ የሞት ጣር ይዞኛል፤ ነፍሴ ግን አልወጣችም፤ እባክህ በላዬ ቆመህ ግደለኝ’ አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ‘ወደ እኔ ቀርበህ ግደለኝ፤ በብርቱ ስለ ቈሰልኩ መሞቴ ነው!’ አለኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፦ ክፉ ጨለማ ይዞኛልና ደግሞ እስካሁን ድረስ ነፍሴ ገና ፈጽማ ሕያውት ናትና በላዬ ቆመህ ግደለኝ አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ሰውነቴ ዝሎአልና፥ ደግሞ እስከ አሁን ድረስ ነፍሴ ገና ፈጽማ ሕያው ናትና በላዬ ቆመህ ግደለኝ አለኝ። |
“መቼም ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፣ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና የክንዱን አንባር ወስጄ እነሆ፤ ለጌታዬ አምጥቻለሁ።”
ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፣ “እነዚህ ሸለፈታሞች መጥተው መሣለቂያ እንዳያደርጉኝ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር ፈቃደኛ አልሆነም፤ ስለዚህ ሳኦል በገዛ ሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።
ወዲያውም ጋሻ ጃግሬውን ጠርቶ፣ “ ‘ሴት ገደለችው’ እንዳይሉ እባክህ ሰይፍህን መዝዘህ ግደለኝ” አለው። ስለዚህ አገልጋዩ ወጋው፤ እርሱም ሞተ።
ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፣ “እነዚህ ሸለፈታሞች መጥተው መሣለቂያ እንዳያደርጉኝ፣ ሰይፍህን መዝዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር፣ ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዚህ ሳኦል በገዛ ሰይፉ ላይ ወድቆ ሞተ።