መዝሙር 32:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በጭንቀት ሰዓት እያንዳንዱ ለአንተ ታማኝ ሰው ወደ አንተ ይጸልይ፤ ብርቱ የመከራ ጐርፍ በሚመጣበት ጊዜ እርሱን አይነካውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የምትታመኑት ሁሉ፣ በጭንቅ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልይ፤ ኀይለኛ ጐርፍ አካባቢውን ቢያጥለቀልቅም፣ እርሱ አጠገብ አይደርስም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ቅዱስ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይለምናል፥ ብዙ የጥፋት ውኃም ወደ እርሱ አይቀርብም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ፤ |
በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመረጥኩት ሰዓት ለጸሎትህ መልስ እሰጥሃለሁ፤ በመዳንም ቀን እረዳሃለሁ፤ ምድሪቱን መልሰህ እንድታቋቋምና ውድማ የሆነውን መሬት እንድታከፋፍል ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ።
እግዚአብሔር፦ “ተስማሚ በሆነ ጊዜ ሰማሁህ! በመዳን ቀን ረዳሁህ!” ስለሚል፥ “እነሆ ተስማሚ የሆነው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳኛው ቀን አሁን ነው።”
ነገር ግን ምሕረት ተደረገልኝ፤ ምሕረት የተደረገልኝም ኢየሱስ ክርስቶስ ወሰን የሌለውን ትዕግሥቱን ከሁሉ የባስሁ ኀጢአተኛ በሆንኩት በእኔ ላይ በማሳየቱ በእርሱ ለሚያምኑና የዘለዓለም ሕይወት ለሚያገኙ ምሳሌ እንድሆን ነው።