ዘወትር በመንገድህ ተራመድኩ፤ ከመንገድህም ወጥቼ አልባዘንኩም።
አረማመዴ በመንገድህ ጸንቷል እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።
የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ።
እግሮቼ እርሱ በሚወደው መንገድ ይሄዳሉ፤ በማወላወል ወደ ግራም ወደ ቀኝም አልልም።
በተስፋ ቃልህ መሠረት አካሄዴን አስተካክል፤ ስሕተትም እንዲሠለጥንብኝ አታድርግ።
ጠባቂህ ዘወትር ንቁ ስለ ሆነ እንድትሰናከል አያደርግህም።
እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቅሃል፤ ሕይወትህንም በሰላም ይጠብቃል።
መረማመጃዬን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤ ሳላጠፋቸውም ወደ ኋላ አልመለስም።
“ጠላቶቼ እኔን በንቀት ዐይን እንዲመለከቱኝ ወይም እግሬን ሲያዳልጠው ራሳቸውን ከፍ እንዲያደርጉ አታድርግ!” ብዬ እለምናለሁ።
ልባችን ለአንተ እምነተቢስ አልሆነም፤ እግራችንም ከአንተ መንገድ አልወጣም።
“ለመውደቅ ተቃርቤአለሁ” ባልኩ ጊዜ እግዚአብሔር ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ደግፎ አቆመኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! ሰው በራሱ ሕይወት እንደማያዝበትና አካሄዱንም በራሱ ሥልጣን መቈጣጠር እንደማይችል ዐውቃለሁ።
“ሰው ድልን የሚያገኘው በኀይሉ ስላልሆነ እግዚአብሔር የታማኞቹን እርምጃዎች ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን ወደ ጨለማ ይጣላሉ።