መዝሙር 16:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚመክረኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በሌሊት እንኳ ሕሊናዬ ያስተምረኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤ በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመከረኝን አምላክ እባርካለሁ፥ ደግሞም በሌሊት ኩላሊቶቼ ይገሥጹኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀኝህን ከሚቃወሟት፥ የሚያምኑብህን የሚያድናቸውን ቸርነትህን ግለጠው። |
በችግር ጊዜ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ሌሊቱን ሙሉ ያለ ዕረፍት እጆቼን ዘርግቼ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ይሁን እንጂ ለመጽናናት አልቻልኩም።
ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።
እናንተን የሚያድን የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፤ “የሚጠቅምህን ሁሉ የማስተምርህና ልትሄድበት የሚገባህን መንገድ የምመራህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ።
ደካሞችን በቃል ማጽናትን ዐውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የምሁርን አንደበት ሰጥቶኛል፤ በየማለዳው ከእንቅልፍ ያነቃኛል፤ እንደ ተማሪም አዳምጥ ዘንድ ጆሮዬን ይከፍታል።
ልጆችዋንም በሞት እቀጣለሁ፤ አብያተ ክርስቲያንም ሁሉ የሰውን ሐሳብና ምኞት የምመረምር እኔ መሆኔን ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደየሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።