እግዚአብሔር ይመስገን! ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።
ሃሌ ሉያ። ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን አመስግኚ።
እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና። ለአምላካችንም ምስጋና ማቅረብ ያማረ ነው።
ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! የእግዚአብሔርን ቅዱስ ስም በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።
በግዛቱ ሁሉ የምትገኙ ፍጥረቶቹ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
ኃጢአተኞች ከምድር ላይ ይጥፉ! ግፍ አድራጊዎችም ይደምሰሱ! ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! እግዚአብሔርን አመስግኚ!
ይህንንም ሁሉ ማድረጉ ሕዝቡ ድንጋጌውን እንዲጠብቁና ሕጉንም እንዲፈጽሙ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን!