የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ እውነተኛ ፈራጅ ነህ፤ ነገር ግን ከጥፋት አምልጠን በሕይወት እንድንኖር ፈቀድክልን፤ እነሆ እኛ፥ በደላችንን ተሸክመን በፊትህ ለመቅረብ የተገባን አይደለንም።”
መዝሙር 130:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአታችንን ብትከታተል ማን ከፍርድ ሊያመልጥ ይችላል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአትን ብትቈጣጠር፣ ጌታ ሆይ፤ ማን ሊቆም ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ኃጢአትን ብትይዝ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመናል። |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ እውነተኛ ፈራጅ ነህ፤ ነገር ግን ከጥፋት አምልጠን በሕይወት እንድንኖር ፈቀድክልን፤ እነሆ እኛ፥ በደላችንን ተሸክመን በፊትህ ለመቅረብ የተገባን አይደለንም።”
ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
በእርሱ ኀይለኛ ቊጣ ፊት መቆም የሚችል ማን ነው? ቊጣውስ እንደ እሳት በነደደ ጊዜ የሚችለው ማነው? እንደ እሳት የሚያቃጥል ቊጣው በሚወርድበት ጊዜ አለቶች ተሰነጣጥቀው ይበታተናሉ።
ነገር ግን እርሱ እንደ ብረት ማቅለጫ እሳትና እንደ ልብስ ማጠቢያ ሳሙና ስለ ሆነ በእርሱ የመምጫ ቀን ጸንቶ መቆም የሚችልና እርሱስ ሲገለጥ በፊቱ መቆም የሚችል ማነው?