ነገር ግን ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ በመቅረብ ቊጣዬን አነሣሥቶ የእስራኤልን ማኅበር እንዳያስፈጅ ሌዋውያን በድንኳኑ ዙሪያ ሰፍረው ይጠብቁት።”
ዘኍል 3:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሜራሪ ጐሣ መሪ የጹርኤል ልጅ አቢኤል ነበር፤ እነርሱም የሚሰፍሩት በድንኳኑ በስተሰሜን ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሜራሪም ጐሣዎች ቤተ ሰቦች አለቃ የአቢካኢል ልጅ ሱሪኤል ይሆናል፤ የሜራሪም ጐሣዎች ከማደሪያው ድንኳን በሰሜን በኩል ይሰፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሜራሪም ወገኖች አባቶች ቤት አለቃ የአቢካኢል ልጅ ሱሪኤል ነበረ፤ እነርሱም በማደሪያው አጠገብ በሰሜን በኩል ይሰፍራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሜራሪም ወገኖች አባቶች ቤት አለቃ የአቢኪያ ልጅ ሱራሔል ነበረ፤ በድንኳኑ አጠገብ በሰሜን በኩል ይሰፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሜራሪም ወገኖች አባቶች ቤት አለቃ የአቢካኢል ልጅ ሱሪኤል ነበረ፤ በማደሪያው አጠገብ በሰሜን በኩል ይሰፍራሉ። |
ነገር ግን ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ በመቅረብ ቊጣዬን አነሣሥቶ የእስራኤልን ማኅበር እንዳያስፈጅ ሌዋውያን በድንኳኑ ዙሪያ ሰፍረው ይጠብቁት።”
የእነርሱም ኀላፊነት በድንኳኑ ተራዳዎችና በመወርወሪያዎቻቸው፥ በምሰሶቹና ምሰሶቹ በሚቆሙባቸው እግሮች፥ እንዲሁም በሌሎች የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ሲሆን፥ በአጠቃላይ እነዚህን ነገሮች በሚመለከት ሥራ ኀላፊነቱ የእነርሱ ነበር።