ዘኍል 23:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ትቢያ ብዛት ያላቸውን የያዕቆብ ዘሮች ማን ሊቈጥር ይችላል ወይስ እንደ አዋራ ብናኝ ብዛት ያለውን የእስራኤልን ሩብ ብዛት ማን ሊገምት ይችላል? የጻድቃንን ሞት እንድሞት አድርገኝ መጨረሻዬንም እንደ እነርሱ አድርገው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የያዕቆብን ትቢያ ማን ቈጥሮ ይዘልቃል? የእስራኤልንስ ሩብ ማን ይቈጥረዋል። የጻድቁን ሞት እኔ ልሙት፤ ፍጻሜዬም የርሱ ዐይነት ፍጻሜ ትሁን!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያዕቆብን ትቢያ ማን ይቈጥራል? የእስራኤልስ አራተኛውን ክፍል ማን ይቈጥራል? የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያዕቆብን ዘር ማን ያውቀዋል? የእስራኤልንስ ሕዝብ ማን ይቈጥረዋል? ሰውነቴም ከጻድቃን ሰውነት ጋር ትሙት፤ ዘሬም እንደ እነርሱ ዘር ትሁን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያዕቆብን ትቢያ ማን ይቈጥራል? የእስራኤልስ እርቦ ማን ይቈጥራል? የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን። |
እንደየክፍላቸው በሮቤል ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት አንድ መቶ ኀምሳ አንድ ሺህ አራት መቶ ኀምሳ ነበር። በዚህ ዐይነት የሮቤል ክፍል ሁለተኛ ተራ ተጓዥ ይሆናል።
እንደየክፍላቸው በኤፍሬም ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት አንድ መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ነበር። በዚህ ዐይነት የኤፍሬም ክፍል ሦስተኛ ተራ ተጓዥ ይሆናል።
እንደየክፍላቸው በዳን ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት አንድ መቶ ኀምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። በዚህ ዐይነት የዳን ክፍል የመጨረሻ ተራ ተጓዥ ይሆናል።
እንደየክፍላቸው በይሁዳ ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበር። በመጀመሪያ የሚጓዘው ይህ ቡድን ነበር።
ይህ እንደ ድንኳን ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊው ሥጋችን ሲፈርስ በሰው እጅ ሳይሆን በእግዚአብሔር የታነጸ ዘለዓለማዊ መኖሪያ በሰማይ እንዳለን እናውቃለን።
ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፤ ይህን ጻፍ፤ “ከእንግዲህ ወዲህ የጌታ ኢየሱስ ሆነው የሚሞቱ የተባረኩ ናቸው!” መንፈስ ቅዱስም “አዎ! ከድካማቸው እንዲያርፉ ሥራቸው ይከተላቸዋል” ይላል።