የልጅ ልጆችህ ወደዚህ ተመልሰው የሚመጡት በአራተኛው ትውልድ ነው፤ እስከዚያ የሚቈዩበትም ምክንያት የአሞራውያን ኃጢአት ገና ስላልተፈጸመ ነው።”
ማቴዎስ 23:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲያውስ አባቶቻችሁ የጀመሩትን እናንተም ፈጽሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ የአባቶቻችሁን ጅምር ተግባር ከፍጻሜ አድርሱ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ፈጽሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ። |
የልጅ ልጆችህ ወደዚህ ተመልሰው የሚመጡት በአራተኛው ትውልድ ነው፤ እስከዚያ የሚቈዩበትም ምክንያት የአሞራውያን ኃጢአት ገና ስላልተፈጸመ ነው።”
ለብዙ ሺህ ሕዝብ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን አሳይተሃል፤ ይሁን እንጂ አባቶቻቸው በሠሩት ኃጢአት ምክንያት ልጆቻቸውን ትቀጣለህ፤ አንተ ታላቅና ኀያል አምላክ ነህ፤ አንተ ሁሉን ቻይና ስምህም የሠራዊት ጌታ ነው፤
“የሰው ልጅ ሆይ! በእነዚህ ሰዎች ላይ ትፈርድባቸዋለህን? ትፈርድባቸዋለህን? እንግዲያውስ አባቶቻቸው ያደረጉትን አጸያፊ ነገር እንዲያውቁ አድርጋቸው።
አሁን ደግሞ እናንተ በአባቶቻችሁ ስፍራ ተተክታችኋል፤ የእግዚአብሔርንም ቊጣ በእስራኤል ላይ ለማምጣት የተዘጋጀ አዲስ ኃጢአተኛ ትውልድ ሆናችኋል።
አሕዛብ የሚድኑበትን ቃል እንዳንናገር እንኳ ይከለክሉናል፤ በዚህ ዐይነት ኃጢአትን በኃጢአት ላይ እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ ስለዚህ በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቊጣ መጥቶባቸዋል።