ሉቃስ 7:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመቶ አለቃው ስለ ኢየሱስ በሰማ ጊዜ የአይሁድ ሽማግሌዎችን “እባካችሁ ኢየሱስ መጥቶ አገልጋዬን እንዲፈውስልኝ ሄዳችሁ ለምኑልኝ፥” ሲል ላካቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ስለ ኢየሱስ በሰማ ጊዜ፣ ባሪያውን መጥቶ እንዲፈውስለት ይለምኑት ዘንድ አንዳንድ የአይሁድ ሽማግሌዎችን ላከበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ኢየሱስም በሰማ ጊዜ የአይሁድን ሽማግሌዎች ወደ እርሱ ልኮ ባርያውን መጥቶ እንዲያድን ለመነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌታችን የኢየሱስንም ነገር በሰማ ጊዜ፥ መጥቶ አገልጋዩን እንዲያድንለት ይማልዱት ዘንድ የአይሁድን ሽማግሎች ወደ እርሱ ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ኢየሱስም በሰማ ጊዜ የአይሁድን ሽማግሎች ወደ እርሱ ላከና መጥቶ ባሪያውን እንዲያድን ለመነው። |
በዚያን ጊዜ አንድ የምኲራብ አለቃ የሆነ፥ ኢያኢሮስ የተባለ ሰው መጣ፤ በኢየሱስ እግር ሥር ወድቆ፥ “እባክህ ወደ ቤቴ ናልኝ፤” ብሎ ለመነው።
እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ምድር ወደ ገሊላ መምጣቱን ሰምቶ ወደ እርሱ ሄደ፤ ወደ ቅፍርናሆም እንዲወርድና በጠና ታሞ ሊሞት የተቃረበውን ልጁን እንዲፈውስለት ኢየሱስን ለመነው።