ሉቃስ 5:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስን፦ “የዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ብዙ ጊዜ ይጾማሉ፤ ይጸልያሉም፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ሁልጊዜ የሚበሉትና የሚጠጡት ለምንድን ነው?” በማለት ጠየቁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አብዛኛውን ጊዜ ይጾማሉ፤ ይጸልያሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንደዚሁ ያደርጋሉ፤ የአንተዎቹ ግን ይበላሉ፤ ይጠጣሉ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አዘውትረው ይጾማሉ፤ ጸሎትም ያደርሳሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለምን በብዙ ይጾማሉ? ጸሎትስ ስለምን ያደርጋሉ? የፈሪሳውያን ወገኖች የሆኑትም ስለምን እንዲሁ ያደርጋሉ? ያንተ ደቀ መዛሙርት ግን ለምን ይበላሉ? ይጠጣሉም?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለ ምን ብዙ ይጦማሉ ጸሎትስ ስለ ምን ያደርጋሉ፥ ደግሞም የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ስለ ምን እንደዚሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም? አሉት። |
“እጆቻችሁን ወደ እኔ ለጸሎት ብትዘረጉ፥ ወደ እናንተ አልመለከትም፤ እጆቻችሁ በደም የተበከሉ ስለ ሆኑ የቱንም ያኽል ልመና ብታበዙ አልሰማችሁም፤
“ሰው ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዳይገባ፥ በሩን የምትዘጉ እናንተ ግብዞች፥ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! እናንተ ራሳችሁ አትገቡበትም፤ መግባት የሚፈልጉትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ!” [
አንድ ቀን ኢየሱስ በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ ጸሎቱንም ባበቃ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ! ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን ጸሎት እንዳስተማራቸው፥ አንተም እኛን መጸለይ አስተምረን!” አለው።
ከዚህም በኋላ ዕድሜዋ ሰማኒያ አራት ዓመት እስኪሆን ድረስ ከቤተ መቅደስ ሳትለይ በጾምና በጸሎት ቀንና ሌሊት እግዚአብሔርን ታገለግል ነበር።
ጌታም እንዲህ አለው፦ “ቀጥተኛ ወደምትባለው መንገድ ሂድ፤ እዚያ በይሁዳ ቤት ሳውል የሚባለውን የጠርሴስ ሰው ፈልግ፤ እርሱ አሁን በጸሎት ላይ ነው።”