ኢያሱ 22:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም በአንድነት ወደ ሴሎ መጥተው በመሰብሰብ በምሥራቅ ነገዶች ላይ ሊዘምቱ ተዘጋጁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነርሱ ላይ ለመዝመት የእስራኤል ማኅበር ሁሉ በሴሎ ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ይህን በሰሙ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ወጥተው እነርሱን ሊዋጉ በሴሎ ተሰበሰቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ይህን በሰሙ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ወጥተው እነርሱን ሊዋጉ በሴሎ ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ይህን በሰሙ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ወጥተው እነርሱን ሊዋጉ በሴሎ ተሰበሰቡ። |
ይህም ከመሆኑ በፊት የእስራኤል ሕዝብ የካህኑን የአልዓዛርን ልጅ ፊንሐስን በገለዓድ ምድር ወደሚገኙት ወደ ሮቤል፥ ወደ ጋድና በምሥራቅ ወደሚኖሩት የምናሴ ነገዶች ሕዝብ ላኩት፤
ከዚህም በኋላ የካህኑ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስና መሪዎቹ በገለዓድ ከሚገኙት ከሮቤልና ከጋድ ሕዝቦች ዘንድ በከነዓን ምድር ወደሚገኙት ወደ እስራኤል ሕዝብ ተመልሰው በመምጣት፥ ያገኙትን ማስረጃ አቀረቡ፤