ኢያሱ 13:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ ኢያሱ በዕድሜ እየገፋ ስለ ሄደ አረጀ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፤ ዕድሜህም ገፍቶአል፤ ገና ብዙ ያልተያዙ ቦታዎች አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱ በሸመገለና ዕድሜው በገፋ ጊዜ፣ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፤ “እነሆ አርጅተሃል፤ ዕድሜህም ገፍቷል፤ ነገር ግን መያዝ ያለበት እጅግ በጣም ሰፊ ምድር ገና አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ሸመገለ ዕድሜውም ስለ ገፋ አረጀ፤ ጌታም እንዲህ አለው፦ “አንተ ሸምግለሃል፥ ዕድሜህም ስለ ገፋ አርጅተሃል፤ ያልተወረሰ እጅግ ብዙ ምድር ገና ይቀራል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ሸመገለ፤ ዘመኑም አለፈ፤ እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፥ “እነሆ ዘመንህ አለፈ፤ ያልተወረሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀርታለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ሸመገለ በዕድሜም አረጀ፥ እግዚአብሔርም አለው፦ አንተ ሸመገልህ፥ በዕድሜህም አረጀህ፥ ያልተወረሰች እጅግ ብዙ ምድር ገና ቀርታለች፥ |
አምላካችሁ እግዚአብሔር በፊታችሁ እየሄደ ይመራችኋል፤ በዚያ የሚኖሩትንም ሕዝቦች ደምስሶ ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እግዚአብሔር በተናገረውም መሠረት ኢያሱ መሪያችሁ ይሆናል።
እስራኤል በምድረ በዳ በጉዞ ላይ ሆኖ ሳለ እግዚአብሔር ሙሴን ይህን ቃል ከተናገረበት ቀን ጀምሮ አሁን እንደምታየኝ እግዚአብሔር እንዳለው ይህን አርባ አምስት ዓመት ጠብቆ አኑሮኛል፤ እነሆ አሁን እኔ ሰማኒያ አምስት ዓመት ሆነኝ።
ስለዚህም ኢያሱ ለእስራኤላውያን እንዲህ አለ፦ “ገብታችሁ የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ምድር ሳትወርሱ የምትቈዩት እስከ መቼ ነው?