ኤርምያስ 2:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ |
“ሂድና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በመጀመሪያ በምድረ በዳ ምንም በማያበቅልበት ትከተሉኝ ነበር፤ በዚያን ጊዜ ሙሽራይቱ ለሙሽራው የምታሳየውን ፍቅርና ታማኝነት ለኔም ታሳይ እንደ ነበረ አስታውሳለሁ።
ሕልም ያለመ ነቢይ ቢኖር ሕልሙን ብቻ ይናገር፤ ቃሌን የሰማ ነቢይ ግን ያንኑ ቃል በታማኝነት ይናገር፤ ገለባ ከስንዴ ጋር ምን ግንኙነት አለው?
እግዚአብሔር የይሁዳ ሕዝብ ወደሚሰግዱበት ወደ ቤተ መቅደሱ የቅጽር በር ላከኝ፤ በዚያ ቆሜ እንድነግራቸው ያዘዘኝ ቃል ይህ ነው፦ “የአኗኗራችሁንና የተግባራችሁን ሁኔታ ለውጡ፤ እኔም በዚህች ምድር እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ፤
የቀድሞውን የወይን ተክል እመልስላታለሁ፤ የመከራንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ፤ እዚያም ከግብጽ ስትወጣ በወጣትነትዋ ወራት በነበራት ሁኔታ በደስታ ትዘምራለች።