ዘፍጥረት 7:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናቡ መዝነብ በጀመረበት ቀን፥ ኖኅና ሚስቱ ከልጆቻቸው ከሴም፥ ከካም፥ ከያፌትና ከሦስቱም ልጆቻቸው ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ዕለት ኖኅና ልጆቹ ሴም፣ ካምና ያፌት፣ እንዲሁም ሚስቱና ሦስቱ የልጆቹ ሚስቶች ወደ መርከቧ ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያውም ቀን ኖኅ፥ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከርሱ ጋር ወደ መርከብ ገቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ፤ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከእርሱ ጋር ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከርሱ ጋር ገቡ። |
እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ብቻ ሆነህ ስላገኘሁህ፥ ከመላው ቤተሰብህ ጋር ወደ መርከቡ ግባ።
ገና በዐይን ስለማይታዩት ነገሮች እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ ኖኅ እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን ለማዳን መርከብን የሠራው በእምነት ነው፤ በኖኅም እምነት ዓለም ኃጢአተኛ መሆኑ ታውቆ ተፈረደበት፤ ኖኅም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወረሰ።
እነዚህ በወህኒ ቤት የነበሩ መናፍስት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው ሳለ አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በዚያ መርከብ ውስጥ ገብተው በውሃ አማካይነት የዳኑት ቊጥራቸው ስምንት የሆነ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።
እንዲሁም የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ሰዎች በነበሩበት ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ሲያመጣ ራርቶ የቀድሞውን ዓለም አልማረውም፤
አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ወደ እናንተ መጥተው ሊቃወሙአችሁ ቢፈልጉ ‘ሚስቶች ለማድረግ የወሰድናቸው በጦርነት አስገድደን ስላልሆነ እባካችሁ ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም በፈቃዳችሁ ስላልሰጣችሁን መሐላችሁን በማፍረስ በደለኞች አትሆኑም’ ብላችሁ መልስ መስጠት ትችላላችሁ።”