ዘፍጥረት 16:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሣራይ አብራምን “እነሆ፥ እግዚአብሔር ልጅ እንዳልወልድ ከልክሎኛል፤ ወደዚህች ወደ አገልጋዬ ግባ፤ ምናልባት በእርስዋ በኩል ልጅ አገኝ ይሆናል” አለችው። አብራምም ሣራይ ባለችው ነገር ተስማማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራምንም፣ “እግዚአብሔር ልጅ እንዳልወልድ አድርጎኛል። ምናልባት በርሷ በኩል ልጆች አገኝ እንደሆን ሄደህ ከአገልጋዬ ጋራ ተኛ” አለችው። አብራምም ሦራ ባለችው ተስማማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦራም አብራምን፦ እነሆ፥ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ፥ ምናልባት ከእርሷ በልጅ እታነጽ እንደሆነ ወደ እርሷ ግባ አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦራም አብራምን፥ “እነሆ፥ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ፤ ከእርስዋ ትወልድ ዘንድ ወደ አገልጋዬ ሂድ” አለችው። አብራምም የሚስቱን የሦራን ቃል ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሦራም አብራምን፤ እነሆ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ ምናልባት ከእርስዋ በልጅ እታነጽ እንደ ሆነ ወደ እርስዋግባ አለችው፤ |
እርስዋን እባርካታለሁ፤ ከእርስዋም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ እባርካታለሁ፤ የብዙ ሕዝቦችም እናት ትሆናለች፤ ከዘርዋም መካከል ነገሥታት የሚሆኑ ይገኛሉ።”
ከሦስቱም እንግዶች አንዱ አብርሃምን “የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች” አለው። እርሱም ይህን በሚናገርበት ጊዜ ሣራ በስተኋላው በድንኳኑ ደጃፍ ቆማ ታዳምጥ ነበር፤
አዳምንም እንዲህ አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘አትብላ’ ያልኩህን ፍሬ ከዛፉ ወስደህ ስለ በላህ፥ አንተ በፈጸምከው ክፉ ሥራ ምክንያት ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ምግብህን ከእርስዋ የምትበላው በብርቱ ድካም ነው።
ጌታው ሚስት የምትሆነው ሴት ሰጥቶት ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወልዳለት ከሆነ ሴትዮዋ ከነልጆችዋ የጌታው ትሁን፤ ሰውየው ግን ብቻውን ነጻ ይውጣ።
በአደባባይ ተቀምጠው የነበሩት ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች እንዲህ አሉ፥ “አዎ፥ እኛ ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ሚስትህን ብዙ ልጆችን በመውለድ የያዕቆብን ቤት እንደ መሠረቱት እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርግልህ፤ እግዚአብሔር በኤፍራታ ያበልጽግህ፤ በቤተልሔምም ዝነኛ ያድርግህ፤