ዳንኤል 6:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛ በመንግሥትህ አስተዳደር ሥራ ላይ የተመደብን የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች፥ ዐቃብያነ ሕግ፥ እንደራሴዎች፥ አማካሪዎችና አገረ ገዢዎች የተስማማንበት አንድ ነገር አለ፤ ይኸውም ከአሁን ጀምሮ እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ወደማንኛውም አምላክ ወይም ሰው ጸሎት እንዳይደረግ ዐዋጅ እንድታስነግር ነው፤ ይህንንም ዐዋጅ የሚተላለፍ ቢኖር በአንበሶች ጒድጓድ እንዲጣል እዘዝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ሆይ፤ እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ወደ አንተ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ ሌላ ሰውም ሆነ ወደ ሌላ አምላክ መጸለይ እንደሌለበት ንጉሡ ዐዋጅ እንዲያወጣ፣ ትእዛዙም እንዲፈጸም፣ ይህንም የተላለፈ ወደ አንበሶች ጕድጓድ እንዲጣል፣ የመንግሥት የበላይ አስተዳዳሪዎች፣ መኳንንት፣ መሳፍንት፣ አማካሪዎችና አገረ ገዦች ሁሉ በአንድነት ተስማምተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመንግሥቱ አለቆች ሁሉ ሹማምቶችና መሳፍንት አማካሪዎችና አዛዦች፦ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ በቀር ማንም እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ልመና ከአምላክ ወይም ከሰው ቢለምን፥ በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ ይጣል የሚል የንጉሥ ሕግና ብርቱ ትእዛዝ ይወጣ ዘንድ ተማከሩ። |
የቆመው ምስል በሚመረቅበት ክብረ በዓል ላይ እንዲገኙ አገረ ገዢዎችን መኳንንትን፥ ሹማምንትን፥ አማካሪዎችን፥ የግምጃ ቤት ኀላፊዎችን፥ ዳኞችን፥ ሌሎችንም የየክፍለ ሀገሩ ባለሥልጣኖችን አስጠራ።
ከዚህ በኋላ አገረ ገዢዎቹ፥ መኳንንቱ፥ አማካሪዎቹ ሁሉ በእነርሱ ዙሪያ ተሰበሰቡ፤ እሳቱ ሰውነታቸውን እንዳልጐዳው፥ ከራስ ጠጒራቸውም አንዲቱን እንኳ እንዳላቃጠለ፥ የመጐናጸፊያቸው መልክ እንዳልተለወጠና ሌላው ቀርቶ የእሳቱ ሽታ እንኳ እንዳልደረሰባቸው ተመለከቱ።
ስለዚህ ዳንኤል ተይዞ መጥቶ ወደ አንበሶች ጒድጓድ እንዲጣል ንጉሡ አዘዘ፤ ዳንኤልንም “ሁልጊዜ በታማኝነት የምታገለግለው አምላክህ ያድንህ” አለው።
አንበሶቹ እንዳይጐዱኝ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አፋቸውን ዘጋ፤ ይህንንም ያደረገው እኔ በእርሱ ዘንድ ንጹሕ መሆኔንና አንተንም አለመበደሌን ስላወቀ ነው።”
ሕዝቤ ሆይ! የሞአብ ንጉሥ ባላቅ ምን እንደ ዐቀደብህና የቢዖር ልጅ በለዓም ምን እንደ መለሰለት አስታውስ፤ ከሺጢም ተነሥተህ ወደ ጌልጌላ በምትሄድበት ጊዜ በመንገድ ላይ የሆነውን ሁሉ አስታውስ፤ ይህን ሁሉ ብታስታውስ አንተን ለማዳን ያደረግኹትን ሁሉ ታውቃለህ።”
አንበሳ ለግልገሎቹ የሚበቃቸውን ያኽል ዐድኖ አመጣ፤ ለእንስቲቱ አንበሳም የምትመገበውን ገድሎ አመጣላት፤ ዋሻውን በታደኑ እንስሶች ጒድጓዱንም በተቦጫጨቀ ሥጋ ሞላ።
ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፥ ከሕግ መምህራን፥ ከሸንጎውም አባሎች ሁሉ ጋር ተማከሩ፤ ከዚያም በኋላ ኢየሱስን አስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።