2 ሳሙኤል 17:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሽራ ወደ ባልዋ እንደምትመለስ ተከታዮቹ በሙሉ ወደ አንተ ተመልሰው እንዲመጡ አደርጋለሁ፤ እንግዲህ አንተ የምትፈልገው አንድ ሰው ብቻ መግደልን ነው፤ የቀረው ሌላው ሕዝብ ግን በሰላም ይኖራል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሳለሁ፤ አንተ የምትፈልገው የአንድ ሰው ብቻ መሞት ሁሉም እንዲመለሱ ያደርጋል። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ በሰላም ይኖራል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሳለሁ፤ አንተ የምትፈልገው የአንድ ሰው መሞት ብቻ ነውና፥ ሕዝቡ ሁሉ በሰላም ይኖራል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሽራ ወደ ባልዋ እንደምትመለስ ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሰዋለሁ፤ የአንድ ሰው ሰውነትን ብቻ ትሻለህና፤ ለሕዝቡ ሁሉ ግን ሰላም ይሆናል፤” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሽራ ወደ ባልዋ እንደምትመለስ ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሰዋለሁ፥ ሕዝቡ ሁሉ ደኅና ይሆናል፥ የምትፈልገው አንድ ሰው ብቻ ነው። |
አበኔርም ዳዊትን “ከአንተ ጋር እንዲነጋገሩና እንዲዋዋሉ አንተም ልብህ በተመኘው ሁሉ ላይ እንድትነግሥ ለማድረግ ወደ እስራኤላውያን ልሂድ” አለው። በዚህም ዐይነት ዳዊት አበኔርን በሰላም አሰናበተው።
ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።