ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁት እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስር ቤት ትቈያላችሁ አለበለዚያ ግን በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።”
2 ሳሙኤል 10:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዐሞናውያን መሪዎች ንጉሡን እንዲህ አሉት፤ “ዳዊት እነዚህን ሰዎች የላከው አባትህን በማክበር የሐዘንህ ተካፋይ ለመሆን ይመስልሃልን? ከቶ እንዳይመስልህ! እርሱ እነዚህን መልእክተኞች የላካቸው በከተማይቱ ላይ አደጋ ለመጣል ያመች ዘንድ እንዲሰልሉለት አይደለምን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሞናውያን መኳንንት ጌታቸውን ሐኖንን፣ “ዳዊት የተሰማውን ሐዘን ለመግለጽ ሰዎች መላኩ አባትህን ለማክበር ዐስቦ ይመስልሃል? የላካቸው ሰዎች ከተማዪቱን እንዲመረምሩ፣ እንዲሰልሉና እንዲያጠፏት አይደለምን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአሞናውያን መኳንንት፥ ጌታቸው ሐኑንን፥ “ዳዊት የተሰማውን ኀዘን ለመግለጽ ሰዎች መላኩ አባትህን ለማክበር አስቦ ይመስልሃል? የላካቸው ሰዎች ከተማዪቱን እንዲመረምሩ፥ እንዲሰልሉና እንዲያጠፏት አይደለምን?” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሞንም ልጆች አለቆች ጌታቸውን ሐኖንን፥ “ዳዊት አባትህን በፊትህ ለማክበር አጽናኞችን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ዳዊትስ ከተማዪቱን ለመመርመርና ለመሰለል፥ ለመፈተንም አገልጋዮቹን የላከ አይደለምን?” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሞንም ልጆች አለቆች ጌታቸውን ሐኖንን፦ ዳዊት አባትህን አክብሮ ሊያጽናናህ ባሪያዎቹን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ዳዊትስ ከተማይቱን ለመመርመርና ለመሰለል ለማጥፋትም ባሪያዎቹን የላከ አይደለምን? አሉት። |
ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁት እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስር ቤት ትቈያላችሁ አለበለዚያ ግን በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።”
ስለ እነርሱ ያየው ሕልም ሁሉ ትዝ አለውና “እናንተ ሰላዮች ናችሁ፤ የመጣችሁትም የአገራችንን ደካማነት እምን ላይ እንደ ሆነ ለመሰለል ነው” አላቸው።
ዐሞናውያን ባለሥልጣኖች ንጉሡን እንዲህ አሉት፤ “ዳዊት እነዚህን ሰዎች የላከው አባትህን በማክበር የሐዘንህ ተካፋይ ለመሆን ይመስልሃልን? ከቶ እንዳይመስልህ! እርሱ እነዚህን መልእክተኞች የላከው ምድሪቱን ወሮ መያዝ ይችል ዘንድ እንዲሰልሉለት ነው።”
ፍቅር ሥርዓተቢስ አያደርግም፤ ፍቅር ያለው ሰው የራሱን ጥቅም ብቻ አይፈልግም፤ ፍቅር ያለው ሰው አይበሳጭም፤ ፍቅር ያለው ሰው ቢበደልም በደልን እንደ በደል አይቈጥርም፤