2 ነገሥት 4:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕፃኑም አደገ፤ በመከር ወራት አንድ ቀን ጧት ያ ልጅ ከአጫጆች ጋር በእርሻ ውስጥ ወደነበረው ወደ አባቱ ሄደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕፃኑ አደገ፤ አንድ ቀንም አባቱ ከዐጫጆች ጋራ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕፃኑም አደገ፤ በመከር ወራት አንድ ቀን ጧት ያ ልጅ ከአጫጆች ጋር በእርሻ ውስጥ ወደነበረው ወደ አባቱ ሄደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕፃኑም አደገ፤ እህል አጫጆችም ወዳሉበት ወደ አባቱ መጣ። አባቱንም፥ “ራሴን ራሴን” አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕፃኑም አደገ፤ አንድ ቀንም እህል አጫጆች ወዳሉበት ወደ አባቱ ወጣ። |
ልጅዋን ከሞት ያስነሣላትን፥ በሱነም ትኖር የነበረችውን ሴት እነሆ፥ ኤልሳዕ አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፥ “እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቈይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ።”
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቦዔዝ ራሱ ከቤተልሔም ተነሥቶ ወደ እርሻው መጣ፤ አጫጆቹንም “እንደምን ዋላችሁ! እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን!” አላቸው። እነርሱም “እግዚአብሔር አንተንም ይባርክህ!” አሉት።