እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርኽን ለአክዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እርሱ እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ።
2 ነገሥት 2:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ! በዚህ ጠንካሮች የሆንን ኀምሳ ሰዎች አለን፤ እንሂድና ጌታህን እንፈልገው፤ ምናልባት የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወስዶ በአንድ ተራራ ላይ ወይም ሸለቆ ውስጥ አሳርፎት ይሆናል።” ኤልሳዕም “አትላኩአቸው” ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ “እነሆ፤ እኛ አገልጋዮችህ እዚህ ዐምሳ ጠንካራ ሰዎች አሉን፤ ምናልባትም የእግዚአብሔር መንፈስ ጌታህን አንሥቶ ከአንዱ ተራራ ላይ አስቀምጦት ወይም ከአንዱ ሸለቆ አግብቶት ይሆናልና እስኪ ሄደው ይፈልጉት” አሉት። ኤልሳዕም፣ “አይሆንም፤ አትላኳቸው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ! በዚህ ጠንካሮች የሆንን ኀምሳ ሰዎች አለን፤ እንሂድና ጌታህን እንፈልገው፤ ምናልባት የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወስዶ በአንድ ተራራ ላይ ወይም ሸለቆ ውስጥ አሳርፎት ይሆናል።” ኤልሳዕም “አትላኩአቸው” ሲል መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “እነሆ፥ ከአገልጋዮችህ ጋር አምሳ ኀ`ያላን ሰዎች አሉ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ዮርዳኖስ ወይም ወደ አንድ ተራራ ወይም ወደ አንድ ኮረብታ ጥሎት እንደ ሆነ፥ ሄደው ጌታህን ይፈልጉት” አሉት። ኤልሳዕም፥ “አትላኩ፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም “እነሆ፥ ከባሪያዎችህ ጋር አምሳ ኀያላን ሰዎች አሉ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወደ አንድ ተራራ ወይም ወደ አንድ ሸለቆ ጥሎት እንደ ሆነ፥ ሄደው ጌታህን ይፈልጉት ዘንድ እንለምንሃለን፤” አሉት። እርሱም “አትስደዱ” አላቸው። |
እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርኽን ለአክዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እርሱ እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ።
ከነቢያቱም ኀምሳው ተከትለዋቸው ወደ ዮርዳኖስ ሄዱ፤ ኤልያስና ኤልሳዕም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ቆሙ፤ ኀምሳውም ነቢያት ደግሞ ጥቂት ራቅ ብለው ቆመው ነበር፤
በእግዚአብሔርም ራእይ ወስዶ በእስራኤል ምድር በአንድ ከፍተኛ ተራራ ላይ አኖረኝ፤ እዚያም አንድ ብዙ ቤቶች የተሠሩበትን ከተማ የሚመስል ከተራራው በስተደቡብ በኩል አየሁ።
እርሱም የሰው እጅ የሚመስል ነገር ወደ እኔ ዘርግቶ የራስ ጠጒሬን ያዘ፤ በዚሁ ራእይ የእግዚአብሔር መንፈስ ከምድር ወደ ሰማይ አነሣኝና ወደ ኢየሩሳሌም አደረሰኝ። በሰሜን በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ በሚያስገባው ቅጽር በር አሳልፎ የእግዚአብሔርን ቅናት የሚቀሰቅስን የጣዖት ምስል ወዳለበት ስፍራ አደረሰኝ።