1 ሳሙኤል 21:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ከሳኦል በመሸሽ አኪሽ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ጋት ንጉሥ ሄደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ዕለት ዳዊት ከሳኦል ሸሽቶ ወደ ጋት ንጉሥ ወደ አንኩስ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያች ዕለት ዳዊት ከሳኦል ሸሽቶ ወደ ጋት ንጉሥ ወደ አኪሽ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ተነሣ በዚያም ቀን ከሳኦል ፊት ሸሸ፤ ወደ ጌትም ንጉሥ ወደ አንኩስ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ተነሣ በዚያም ቀን ሳኦልን ፈርቶ ሸሸ፥ ወደ ጌትም ንጉሥ ወደ አንኩስ ሄደ። |
ንጉሥ ኢዮአቄምና መኳንንቱ፥ እንዲሁም የጦር አዛዦቹ ኡሪያ የተናገረውን በሰሙ ጊዜ፥ ኡሪያ እንዲገደል ንጉሡ ፈለገ፤ ኡሪያ ግን ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ፤ ወደ ግብጽም ሸሽቶ አመለጠ፤
ወደ እርሱም ሮጦ በመሄድ በላዩ ላይ ቆመ፤ የጎልያድንም ሰይፍ ከሰገባው በመምዘዝ ራሱን ቈረጠው። ፍልስጥኤማውያንም የእነርሱ ዝነኛ ተዋጊ ጎልያድ መገደሉን ባዩ ጊዜ ሸሹ።
ዳዊትም ምን ማድረግ እንደሚገባው አቤሜሌክ እግዚአብሔርን ጠይቆለታል፤ ከዚያም በኋላ ለዳዊት ጥቂት ምግብና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጥቶታል” ሲል ተናገረ።