ወይም ያልታወቁና እንግዳ የሆኑ፥ ቁጡና እሳት የሚተፉ፥ ወይም የሚከረፋ ጢስ የሚተፋ፥ ወይም ከአይኖቻቸው አስፈሪ ብልጭታን የሚወረውሩ፥
ዓለምን ካለመኖር ለፈጠረ ሁሉን ለሚችል ቀኝ እጅህ ብዙ ድቦችንና ቍጡ አንበሶችን ትልክባቸው ዘንድ አይሳነውምና።