ተክሎች የማይበስል ፍሬ ከተሸከሙበት፥ ላላመነች ነፍስ የቆመው መታሰቢያ የጨው ዓምድ ሆኖ ከቀረበት፥ በአምስቱ ከተሞች ላይ ከወረደው እሳት ሸሽቶ እንዲያመልጥ ረድታዋለች።
ለክፋታቸው ምስክር ልትሆን እስከ ዛሬ ድረስ ምድረ በዳ ሆና እየጤሰች አለች፥ ተክሎችዋም በጊዜዋ ቢያፈሩ ፍጹማን ያልሆኑ ናቸው፤ ያላመነች ሰውነትም መታሰቢያ ሆኖ የሚታይ የጨው ድንጋይ ሆና ቆማለች።