ሰዎች ክፉ በመፈጸም ሲያድሙ፥ እንዲበጣበጡ ተፈረደባቸው፤ ያንጊዜ ጻድቁን ሰው ለየች፤ በእግዚአብሔርም ፊት አቀረበች፤ ከልጁም ኀዘን አበረታችው።
አሕዛብ ወደ ተለያየ ክፋትና ጥመት ተጨልጠው በሄዱ ጊዜ ጻድቁን አመለከተችው፤ ያለ በደልና ያለ ነውር ለእግዚአብሔር ጠበቀችው፤ በቸርነትም የጸና ልጁን ጠበቀች።