መጽሐፈ ጥበብ 10:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወንድሙ ቁጣ የሚሸሸውን ጻድቅ ሰው፥ በቀና መንገዶች መራችው፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት አሳየችው፤ ስለ ቅዱስ ነገሮችም ያውቅ ዘንድ አስተማረችው፤ ድካሙ ፍሬ እንዲያፈራ አደረገች፤ የጥረቱንም ዋጋ ሰጠችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህች ከወንድሙ ቍጣ የተነሣ የሸሸውን ጻድቅ ሰው ወደ ቀና መንገድ መራችው። የእግዚአብሔርንም መንግሥት አሳየችው፤ የተቀደሱትንም ማወቅን ሰጠችው፥ ከድካሙ የተነሣም አበለጸገችው፥ ጥሪቱንም አበዛችለት። |