የሴት ልጅ ውበት ተመልካቹን ያስደስታል፤ ወንድ ከዚህ የተሻለ የሚወደው ነገር የለም።
የአሮንንም በረከት በሕዝብህ ላይ አሳድር፤ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ዘለዓለማዊ አምላክ እግዚአብሔር አንተ ብቻ እንደ ሆንህ ይወቁ።