ለኃጢአት ስርየት የሚጾም ሰው፥ ዳግም የሚበድል ከሆነም እንዲሁ ነው። የዚያን ሰው ጸሎት ማን ይሰማዋል? ራስን ማዋረድ ምን ይጠቅማል?
የሰው ሕይወቱ ወይን መጠጣት ነው፤ መጥኖ ለሚጠጣውም ሰው ደስታ ነው፤ እርሱ ለሰው ደስታ ሊሆን ተፈጥሯልና ወይን ለማይጠጣ ሰው ሕይወቱ ምንድን ነው?