ከድሆች ሀብት ተነጥቆ የሚቀርብ መሥዋዕት፥ ልጁን በአባቱ ፊት እንደ መሠዋት የከፋ ነው።
መጥኖ የሚመገብ ሰው እንቅልፉ ጤና ነው፤ ከእንቅልፉም በጧት በነቃ ጊዜ ሆዱን አይከብደውም፤ ለማይጠግብ ለስሱ ሰው በሽታው ቍንጣን፥ ጓታና ብስና ነው።