በራት ግብዣው ላይ ያዋርድሃል፥ ሁለቱ ወይም ሦስቱ ያለህን ካሟጠጠ በኋላ ይስቅብሃል፤ ከዚህ በኋላ ባየህ ቍጥር ፊቱን ይመልስብሃል፥ ራሱን ይነቀንቅብሃል።
በመብሉም ይሸነግልሃል፤ አንድ ጊዜ፥ ሁለት ጊዜ፥ ሦስት ጊዜም ያስትሃል፤ ከዚህም በኋላ እንደማይሰማህ ወደ ኋላ ይመለሳል፤ ቢያይህም ይሥቅብሃል፤ ራሱንም ይነቀንቅብሃል።