ሀብታም ሲናገር ሁሉም ያዳምጣል፤ ንግግሩንም ከፍ ከፍ ያደርጉለታል። ድኃ ሲናገር ይህ ማነው ይባላል፤ ቢደናቀፍም ገፍተው ይጥሉታል።
ኀጢአት ሳትሠራ ባለጸግነት መልካም ነው፤ ኃጥእ ድህነቱን ባፉ ያክፋፋታል።